‘ልጄን በደንብ ያወቅኳት በማስታወሻዋ ነው’ የአና ፍራንክ አባት ኦቶ ፍራንክ - BBC News አማርኛ (2024)

‘ልጄን በደንብ ያወቅኳት በማስታወሻዋ ነው’ የአና ፍራንክ አባት ኦቶ ፍራንክ - BBC News አማርኛ (1)

የፎቶው ባለመብት, Alamy

የአና ፍራንክ ማስታወሻ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው እአአ ሰኔ 25/1947 ነበር። በወቅቱ በዓለም ላይ እጅግ የተወደደ እና ብዙ ሽያጭ የነበረው መጽሐፍ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ የበርካቶችን ቀልብ እንደያዘ ነው።

ታዳጊዋ አና ከሞተች አስርት ዓመታት ቢቆጠሩም፣ የናዚን ጭፍጨፋ ሽሽት በተደበቁበት ምሥጢራዊ ቤት ሆና በጻፈቻቸው የቀን ውሎ ማስታወሻዎቿ ህያው ነች።

ከቤተሰቡ ሁሉ ከናዚ ግፍ የተረፉት አባቷ ኦቶም “ልጄን ይበልጥ ያወቅኳት በማስታወሻዎቿ ነው” ሲሉ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ኦቶ ከቤተሰባቸው ጋር ተለያይተው ከቆዩ በኋላ የቤተሰባቸውን ሁኔታ ለማወቅ ወደ አምስተርዳም በሄዱበት ጊዜ ነበር ጓደኞቻቸው ጠብቀው ያቆይዋቸውን የአናን የውሎ ማስታወሻዎች የሰጧቸው።

ጓደኞቻቸው ማስታወሻዎቹ በመጽሐፍ መልክ እንዲታተሙ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው።

የአና አባት ኦቶ ፍራንክ መጀመሪያ ላይ የልጃቸውን ማስታወሻ ለማሳተም ይቅርና ለራሳቸውም ለማንበብ አቅም አጥተው ነበር። የማሳተም ውሳኔ ላይ ለመድረስም ጊዜ ወስዶባቸዋል።

ኦቶ በ1976 ወደ የቢቢሲ የሕፃናት የቴሌቪዥን ፕሮግራም ብሉ ፒተርስ ስቱዲዮ በማቅናት የሚወዷትን ልጃቸውን የግል ማስታወሻ ለምን ማሳተም እንደፈለጉ ተናግረዋል።

“ልጄን ያወቅኳት በማስታወሻዋ ነው” ሲሉም ለጋዜጠኛ ሌስሊይ ጁድ አስረድተዋል።

ኦቶ መጀመሪያ ላይ ለአስደናቂዋ ልጃቸው መጻፊያ ደብተር የሰጧት እአአ ሰኔ 12/1942 ለተከበረው የ13ኛ ዓመት የልደት በዓሏ ስጦታ ነበር።

ሆኖም አና ልክ ለቅርብ ጓደኛዋ ምሥጢር እንደምታጫውት እያደረገች በውስጧ ያለውን ሃሳብ ለማስፈር ልትጠቀምበት የወሰነችው ወዲያውኑ ነበር።

ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፈችበትም ሰኔ12/1942 ነበር።

አና ለመጀመሪያ ጊዜ በማስታወሻዋ ላይ ያሰፈረችው ጽሑፍም “ከዚህ በፊት ለማንም የማልነግረውን እና የማላደርገውን ሁሉ ምንም ሳልደብቅ ለአንቺ እንደምነግርሽ ተስፋ አደርጋለሁ። አንቺም ጥሩ ደጋፊዬ እና አጽናኜ እንደምትሆኝ ተስፋ አለኝ” የሚል ነበር።

  • ዓለም ዛሬም ያልረሳት አና ፍራንክ በናዚዎች ከተያዘች በኋላ ምን ደረሰባት?

  • አና ፍራንክን ለናዚ አሳልፎ የሰጣትን ሰው ማንነት ያጋለጠው መጽሐፍ እየተተቸ ነው

  • የአና ፍራንክን ቤተሰብ ለናዚ አሳልፎ የሰጠ ተጠርጣሪ በአዲስ ጥናት ተለየ

የናዚ ፓርቲ በጀርመን ፌደራላዊ ምርጫ ማሸነፉን እና አዶልፍ ሂትለር መራሔ መንግሥት ሆኖ መመረጡን ተከትሎ የአና አባት ኦቶ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አና ከተወለደችበት ፍራንክፈርት ወደ አምስተርዳም ያቀኑት እአአ በ1933 ነበር።

የናዚ ፓርቲ መሪ አዶልፍ ሂትለር ለጀርመን ችግሮች በአጠቃላይ አይሁዳውያንን ተጠያቂ በማድረግ ይታወቃል።

ፓርቲው ሥልጣን ሲጨብጥም አይሁዳውያንን ማንገላታት ያዘ።

የአና ቤተሰቦች ደኅንነታችን ይጠበቃል ብለው ወደ ኔዘርላንድስ፣ አምስተርዳም ሸሹ።

አና ትምህርት ቤት ገባች። አዳዲስ ጓደኞች አፈራች። የደች ቋንቋን ተማረች።

የ10 ዓመት ልጅ ሳለች፣ መስከረም 1/1939 ጀርመን ፖላንድን ወረረች። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተቀሰቀሰ።

ከአንድ ዓመት በኋላ ጀርመን ኔዘርላንድስን ወረረች። ናዚዎች አይሁዳውያንን ማሳደዱን ገፉበት።

አይሁዶች የግላቸው የንግድ ድርጅት እንዳይኖራቸው ተከለከሉ። ለመለየትም ቢጫ የኮከብ ምልክት ያለው ልብስ እንዲያደርጉ ተገደዱ። የሰዓት እላፊም ተጣለባቸው።

ኦቶ ልክ እንደ ሌሎች አይሁዶች ሁሉ እአአ ከ1938 ጀምሮ ወደ አሜሪካ ለመሰደድ ጥረት ሲያደርጉ ነበር የቆዩት።

ሆኖም በጥገኝነት ፖሊሲ ምክንያት እና ሒደቱ ረዥም ጊዜ በመውሰዱ ቪዛ ማግኘት አልቻሉም ነበር።

ናዚ በተቆጣጠራቸው ሁሉም አገራት የሚገኙ የአሜሪካ የቆንስላ ቢሮዎችን እአአ ሐምሌ1941 ከመዝጋቱ በፊት ወረቀታቸው ማለቅ አልቻለም ነበር።

‘ልጄን በደንብ ያወቅኳት በማስታወሻዋ ነው’ የአና ፍራንክ አባት ኦቶ ፍራንክ - BBC News አማርኛ (3)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

እአአ 1942 ከአና ልደት አንድ ወር በኋላ የኦቶ ታላቋ ልጃቸው ማርጎት የጀርመን የሠራተኞች ካምፕ ውስጥ እንድትሠራ ታዘዘች።

ባለሥልጣናቱን ለመሸሽም መላ ቤተሰቡ ኦቶ በአምስተርዳም ይሠሩበት ከነበረው የንግድ ተቋሙ ፎቅ ላይ ፈልገው ባገኙት አንድ ምሥጢራዊ ቤት ውስጥ ተደበቁ።

የፍራንክ ቤተሰቦች ከሌላ ቤተሰብ እና ከቤተሰብ ጓደኛ ጋር በመሆን በዚያች አነስተኛ ምሥጢራዊ ቤት ውስጥ ለሁለት ዓመታት ተደብቀው ቆዩ።

ቀን ቀን ማውራት አይችሉም ነበር። እስከሚመሽ እና ቢሮው ጸጥ እስከሚል ድረስ ድምጻቸው እንዳይሰማ በማሰብ መጸዳጃ ቤትም አይጠቀሙም።

ምግብ እና መጠጥ ይገባላቸው የነበረውም ታማኝ በሆኑ ረዳቶች አማካኝነት ነበር።

በዚህ ሁሉ ጊዜያት አና ሃሳቦቿን እና የየዕለት ውሎዋን በማስታወሻዋ ላይ ታሰፍር ነበር። እኩዮቿን በመናፈቅም እንደ ኪቲ ያሉ ምናባዊ ጓደኞችን ፈጠረች።

ጭንቀቷን፣ ስጋቷን፣ ምኞቷን፣ መሰላቸቷን እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በትንሽ ክፍል መኖሯ የፈጠረባትን ስሜት በማስታወሻዋ ላይ አስፍራለች።

አና ለመጨረሻ ጊዜ በውሎ ማስታወሻዋ የጻፈችው ወደ ግዳጅ ማቆያው ከመወሰዳቸው ከሦስት ቀናት በፊት ነው። ጊዜው ደግሞ እአአ ነሐሴ 1/1944 ነበር።

ነሐሴ 4 ጠዋት ላይ የተደበቁበት ቤት ተወረረ። በቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎችም ተይዘው ታሰሩ።

ናዚዎች መጠለያውን እንዴት እንደደረሱበት እስካሁን አይታወቅም።

ነሐሴ 4/1944 ተደብቀው የነበሩትን ሰዎች ወደ ኦሽዊትዝ-ቢርካኑ የግዳጅ ማቆያ ከተቷቸው።

ኦቶ ከባለቤታቸው ኤዲት፣ ከታላቅ ሴት ልጃቸው ማርጎት እና አና ጋር ተለያዩ። ሦስቱም በግዳጅ ማቆያው ውስጥ ቆዩ።

ከጊዜ በኋላ ከእህቷ ጋር ወደ በርገን ቤልሰን የግዳጅ ካምፕ የተዛወረችው አና ካምፑ ነጻ ከመውጣቱ ጥቂት ሳምንታት በፊት በመጋቢት 1945 በታይፈስ ምክንያት ሕይወቷ አለፈ።

አስገራሚ ፅናት እና ሰብዓዊነት

ኦቶ ጦርነቱ ካበቃ በኋላ የቤተሰባቸውን መጨረሻ ለማወቅ ወደ አምስተርዳም ተመልው ሄዱ። ከቤተሰባቸው በሕይወት የተረፉት ብቸኛው ሰው ነበሩ። እጅግ ነበር ያዘኑት።

የአናን ማስታወሻዎች እና ደብዳቤዎች ግን ጓደኞቻቸው ሜፕ ጊስ እና ቢፕ ቮስኩጂል ታድገዋቸዋል። ወደ አምስተርዳም በተመለሱ ጊዜ እነዚህን ማስታወሻዎች በክብር አስቀምጠው የሰጧቸውም እነርሱ ናቸው።

በሐዘን የተዋጡት ኦቶ ማስታወሻዎቹን መመልከት አልቻሉም ነበር።

ነሐሴ 22 ስዊትዘርላንድ ለሚገኙት እናታቸውም “ለማንበብ ብርታት አጣሁ” ሲሉ ጽፈውላቸው ነበር።

ኦቶ በመጨረሻ ጥንካሬውን አግኝተው ማስታወሻዎቹን ባነበቧቸው ጊዜ ጽሑፎቹ ዐይን ገላጭ ሆነው ነበር ያገኟቸው።

ጽሑፎቹ በአስፈሪ እና አስደንጋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ብልህና አርቆ አሳቢ የነበረችውን ታዳጊ ልጃቸውን አዕምሮ የተመለከቱበት መስኮት ሆነው ነበር ያገኟቸው።

ከእናቷ ጋር የነበራትን ግጭት፣ በእህቷ ላይ ያላትን ቅሬታ፣ ስለ ራሷ ያላትን ግምት፣ ስለ አካላዊ ለውጧ በዝርዝር ያትታሉ።

አብረዋቸው ከሚኖሩ ሌሎች ሰዎች ጋር ስላላት ግንኙነት፣ በምሥጢራዊ ቤቱ ውስጥ ስላለው ፀጥታ እና ተገልሎ መኖር እንዴት አስጨናቂ እንደሆነ ትገልጻለች።

“ጎጆ ውስጥ እንዳለ ክንፉ እንደተሰበረ ዘማሪ ወፍ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል” ስትል ነበር የነበረችበትን ሁኔታ የገለጸችው።

ጽሑፎቿ እያለፈችበት የነበረውን አስከፊ ሕይወት የሚገልጹ ቢሆንም፣ ኦቶ በጽሑፎቹ ውስጥ ትንሽም ቢሆን የልጃቸውን ደስታ ማየት ችለዋል።

በመስኮቷ ስለምትመለከተው ተፈጥሮ፣ በድብቅ ቤቱ ውስጥ አብሯቸው ይኖር ከነበረው ፒተር ቫን ዳን ጋር ስለነበራት ፍቅር የጻፈችው ፈገግ የሚያስብሉ ነበሩ።

አና በስዊትዘርላንድ በበረዶ ላይ ስለመንሸራተት ህልሟ፣ ስለ ማንነቷ፣ ከእውነተኛ እና ከምናባዊ ጓደኞቿ ጋር ስላላት ግንኙነት፣ ሃሳቦቿን ለማሳተም ስለነበራት ምኞቶቿም በማስታወሻዋ ላይ አስፍራለች።

አባቷ ኦቶ የአና ውስብስብ እና ምናባዊ አስተሳሰብ ምን ያህል በሳል እንደነበር የተረዱትም ማስታወሻውን ካነበቡ በኋላ ነበር።

ኦቶ ከሁሉም በላይ የአናን የጽሑፍ ተሰጥኦ፣ አስጨናቂ ሁኔታን ለመጋፈጥ የነበራትን ያልተለመደ ድፍረት እና ሰብዓዊነት ያደንቃሉ።

“ማስታወሻውን ካነበብኩት በኋላ ኮፒ አድርጌ ሁላችንንም ለሚያውቁን ጓደኞቻችን ሰጠኋቸው” ሲሉም እአአ በ1976 ከቢቢሲዋ ጁዲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

ከጓደኞቻቸው አንዱ በማተሚያ ቤት ተቀጥሮ ይሠራ ነበር።

“‘ማስታወሻውን እንደ ግል ንብረትህ ይዘህ የመቆየት መብት የለህም። ይህ የሰው ልጆች ታሪክ ነው። ማሳተም አለብህ’ አለኝ ከዚያም አሳተምኩት” ብለዋል።

ከዚያም እአአ ሰኔ 1947 የአና ማስታወሻዎች የተወሰኑ የቋንቋ እና መሰል እርማቶች ተደርገውበት ‘Het Achterhuis’ ወይም ‘The Secret Annex’ በሚል ታተመ።

መጽሐፉ በጣም ስኬታማ የነበረ ሲሆን የናዚዎችን የዘር ማጥፋት ጭካኔ ፍንትው አድርጎ ለዓለም የገለጠ ነበር።

እአአ በ1952ም ‘አና ፍራንክ፡ ዘ ዲያሪ ኦፍ ኤ ያንግ ገርል’ በሚል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ታትሟል።

በ1956 የፑሊተዘር ሽልማት አሸናፊ የሆነ ሲሆን ከሦስት ዓመታት በኋላ በፊልም ተሠርቷል።

የአና ቃላቶች በአጭር ከተቀጩ ሕይወቷ በላይ የኖሩ ናቸው። መጽሐፏ አማርኛን ጨምሮ በ70 ቋንቋዎች የተተረጎሙ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ የዓለምን አንባቢዎች ቀልብ እንደያዘ ነው።

መጽሐፉን በማሳተማቸው እና የልጃቸውን ግላዊ ሃሳቦች በማውጣታቸው የተቆጩበት አጋጣሚ ይኖር እንደሆነ በቢቢሲ የተጠየቁት ኦቶም “ምንም አልጸጸትም፤ ምክንያቱም አና ከማስታወሻዎቿ በአንዱ ‘ከሞትኩም በኋላ መኖር እፈልጋለሁ’ ብላለች። በመሆኑም በተወሰነ መንገድም ቢሆን በብዙዎች ልብ ዘንድ እየኖረች ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከናዚ ወታደሮች ተደብቃ የጻፈችው የውሎ ማስታወሻ የታተመው ሕይወቷ በናዚ ካምፕ ውስጥ ካለፈ ከሰባት ዓመታት በኋላ ነው።

አና ያኔ ትኖርበት የነበረው ቤት ዛሬ ላይ የቱሪስት መዳረሻ ነው። ለሕዝብ ዕይታ ከተከፈተ ዘንድሮ 64ኛ ዓመቱን ይዟል።

‘ልጄን በደንብ ያወቅኳት በማስታወሻዋ ነው’ የአና ፍራንክ አባት ኦቶ ፍራንክ - BBC News አማርኛ (2024)
Top Articles
Latest Posts
Article information

Author: Jonah Leffler

Last Updated:

Views: 6392

Rating: 4.4 / 5 (45 voted)

Reviews: 92% of readers found this page helpful

Author information

Name: Jonah Leffler

Birthday: 1997-10-27

Address: 8987 Kieth Ports, Luettgenland, CT 54657-9808

Phone: +2611128251586

Job: Mining Supervisor

Hobby: Worldbuilding, Electronics, Amateur radio, Skiing, Cycling, Jogging, Taxidermy

Introduction: My name is Jonah Leffler, I am a determined, faithful, outstanding, inexpensive, cheerful, determined, smiling person who loves writing and wants to share my knowledge and understanding with you.